Write your awesome label here.
Write your awesome label here.
Write your awesome label here.

እንኳን ወደ እንግሊዝኛ ትምህርት በደህና መጣችሁ!

ወጣቶች ስራ ፈጣሪዎች በዋናነት ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ልዩ ችግሮች ለመፍታት በሚያግዙ ፈጠራዎች ለወጣቶች በሚስማማ መልኩ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ የፈጠራ ስራ ነው።

እንግሊዝኛ አለም-ዓቀፍ ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን በአብዛኛዎቹ አገሮች ውስጥ ለመስራት እና መረጃን ለማግኘት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ከመቼዉም ጊዜ እያየለ መጥቷል።

የእንግሊዝኛ ቋንቋን አጓጊ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለወጣቶች በማቅረብ በአፍ መፍቻ ቋንቋችው ልክ በእንግሊዘኛን እንዲግባቡ እና የተወሳሰቡ ሃሳቦችዎን በቀላሉ እንዲገልጹ የሚያግዝ መማሪያን አቅርበንላችኋል። 

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታችሁን ለማሳደግ የምናደርገዉን የትምህርት ጉዞ አብረን እንጀመራለን። ሥርዓተ-ትምህርታችን በእውነተኛ ህይወት ሁኔታዎች ላይ በማተኮር የሰዋስው፣ የቃላት አነጋገር እና የቃላት አጠራርን ጨምሮ ሁሉንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ መሰረታዊ ክህሎት እና እውቀቶችን ይሸፍናል።

ተልዕኳችን

ቋንቋ እና ሌሎች ገዳቢ እንቅፋቶችን ለመፍታ የሚያግዙ ትምህርታዊ ይዘቶችን በማበልፀግ የወጣቶችን የስራ ፈጠራ እና ችግር ፈቺነት ክህሎት ማሳደግ እንዲሁም ወጣቶችን በእውቀት አና አመለካከት በማላቅ የማህበረሰብ ለውጥ ማምጣት።

ልዩ የሚያደርገን ምንድን ነው?

ተደራሽነት

የአንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን ማሻሻል ለሚፈልጉ ሁሉ ቦታ ጊዜ እና ሁኔታ ሳይገድባቸው በእጅ ስልካቸው ቅርበት መማር ማስቻላችን  

 ከህይወት እንቅስቃሴዎች ጋር አያይዘን ማቅረባችን

የዕለት ከዕለት ውይይቶች፣ስራን፣ እንቅስቃሴን እና ሙያዊ ስኬትን ለማዳበር በሚረዱ የቋንቋ ዘርፎች ማካተታችን።

ሳይንሳዊ ዘዴ መከተላችን

ዓለም ዓቀፍ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ሳይንሳዊ የቋንቋ መማሪያ ስልቶችን ተከትለን የትምህርት ይዘቶች ማበልጸጋችን።  

ምቹ አቀራረብ፡

በማንኛዉም የ ስራ እና የአኗኗር ዘይቤ ዉስጥ ለሚገኙ ወጣቶች በሚስማማ መልኩ ተዘጋጅቶ መቅረቡ። 
Write your awesome label here.
ይህ በዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ ወደ እናንተ የቀረበ
መማሪያ ነው። በጋራ፣ በሁሉም ዕድሜ ላሉ ተማሪዎች ቋንቋ መማርን አስደሳች እና የሚያበለጽግ ለማድረግ እንተጋለን።
Created with